የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሰሜን ግንባር ለተመለሱ የጋምቤላ ክልል የፖሊስ አባላት የጀግና አቀባበል አደረገላቸው።

January 15, 2023 (GSN) - Well-deserved welcoming heroes’ recognition and appreciation to Gambella’s own special forces in uniform from the Ethiopian Federal Police.

Thank you all for defending and serving your community and your country. Job well-done and congratulation to all.

ክቡር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት ጀግኖች የፖሊስ አባላትን በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት ተቀብለው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከሕዝብና መንግሥት የተጣለባችሁን አደራና ኃላፊነት በጥሩ ዲሲፕሊንና ብቃት ስለተወጣችሁ በተቋሙና በራሴ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ላቀርብላችሁ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

የቀረበላቸውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው ወደኋላ ሳይሉ የተሰጣቸውን ግዳጅ በጀግንነት ለፈፀሙት የፖሊስ አባላት በእያንዳንዱ ሥም የተዘጋጀ የዕውቅና ሰርተፊኬት እንደሚሰጣቸውም ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ተናግረዋል።

ከለውጥ በፊት ፖሊስ እንደሀገር በትብብር ከመስራት ይልቅ የአንዱ ክልል ፖሊስ ከሌላው የክልል ፖሊስ ጋር የማይግባባበት ሁኔታ እያመዘነ እርስ በርስ ወደ ግጭት ይገባ እንደነበረ ያስታወሱት ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አሁን ላይ የነበረው ችግር ተቀርፎ መላው የኢትዮጵያ ፖሊስ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስተባባሪነት በአዲስ ምዕራፍ በአንድ የፖሊስ አርማና መሪ-ቃል በተሰማራበት ግዳጅ ሁሉ በትብብር መንፈስ፣ በአንድነት፣ በቁርጠኝነትና በታማኝነት አብሮ መስራት በመቻሉ በሀገር ደረጃ የፀጥታውን ሥራ ውጤታማ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡

አያይዘውም ፖሊስ በዘር፣ በሃይማኖትና በቋንቋ ልዩነት ሳያደርግ የትም ቦታ በማንኛውም ጊዜ የሚሰራ ሙያ በመሆኑ ወደ ክልላችሁ ስትመለሱም እንደ ክልል ብቻ ሳይሆን እንደሀገር እያሰባችሁ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል በእኩልነት ማገልገል እንዳለባቸው ተናግረው የኢትዮጵያ ፖሊስ ከዚህ በኋላ በሠፈር ብቻ የታጠረ ሳይሆን በየትኛውም ቦታ ፖሊሳዊ አገልግሎት የሚሰጥና እንደወታደርም የትኛውንም መስዋዕትነት ከፍሎ ሀገሩን ከማንኛውም የፀጥታ ችግር የሚታደግ መሆኑን አስመስክራችኋል ብለዋል፡፡

ከለውጡ በኋላ የኢትዮጵያ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር በፖሊሳዊ ሙያ እና በሪፎርሙ ውስጥ በተፈጠረው አንድነት እየተመራ ሀገራችን ከነበረችበት የፀጥታ ችግር እንድትወጣ ሁሉም የፌደራል፣ የክልል እና የከተማ ፖሊስ እርስ በርስ በመተባበር በዚያ ወሳኝ ጊዜ ውስጥ ተቀናጅተው በመስራት የህይወት መስዋዕትነት ጭምር በመክፈል ሀገራችንን ወደ ተሻለ ሰላም በማሸጋገርና በማጽናት በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ጭምር ተምሳሌት እንደሆነ ገልፀዋል።

በግዳጅ ላይ እያላችሁ ከሌሎች የትግል ጓዶች የቀሰማችሁትን ልምድና ተሞክሮ በአግባቡ ተጠቅማችሁ፤ የራሳችሁንም የዳበረ ፖሊሳዊ ስነ-ምግባር ጨምራችሁ በክልላችሁ የተሻለ የፀጥታ ሥራ እንድትሰሩ በማለት ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አባላቱን አሳስበዋል፡፡ Source: Ethiopia Federal Police

 

Connect with us